Latest Entries »

ሶስት ሰዎች በፍቅር እና በወንጀል አብረው ያደሩበት በአዲስ አበባ ሆቴል የተፈጸመ ታሪክ እና አዲስ አበባ ውስት እየተስፋፋ የመጣ አለም አቀፋዊ የወሲብ ንግድ

ጥሩነሽ ዲባባ

ጥሩነሽ ዲባባ

ዛሬ በተካሄደው ታዋቂው የለንደን ማራቶን ላይ የተሳተፈችው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 2 ሰአት ከ20 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት የመጀምሪያ የማራቶን ውድድሯን በሶስተኛነት አጠናቃለች። ከባድ ከሚባሉ የማራቶን ውድድሮች አንዱ በሆነው በዚህ ማራቶን ውድድር ኢድና ኪፕላጋት እና ፍሎረንስ ኪፕላጋት የተባሉ ኬንያውያን ከጥሩነሽ በ14 እና በ11 ሰከንድ ቀድመው በመግባት አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነው አጠናቀዋል። እስካሁን በአብዛኛው በ5ሺ እና 10ሺ ውድድሮች ላይ ብቻ ተወዳዳሪ የነበረችው ጥሩነሽ ከውድድሩ በኋላ እንደ መጀመሪያ ማራቶንነቱ በውጤቷ ደስተኛ መሆኗን እና ወደፊት በሚካሄዱ የማራቶን ውድድሮች ላይ እንደምትሳተፍ ለጋዜጠኞች ተናግራለች። ጥሩነሽን በመከተል ፈይሴ ታደሰ እና አበሩ ከበደ 4ኛ እና 5ኛ ሆነው ሲጨርሱ የለንደን ኦሎምፒክ የማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ቲኪ ገላና ውድድሩን በ9ኛነት አጠናቃለች።

በወንዶቹ ውድድርም የመጀመሪያ ማራቶኑን የሮጠው በትውልድ ሶማሊያዊ በዜግነት እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ ውድድሩን በ8ኛነት ሲያጠናቅቅ በዚህ ውድድር ጸጋዬ ከበደ፣ አየለ አብሽሮ እና ጸጋዬ መኮንን ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድሩን ጨርሰዋል። ሌላው ኢትዮጲያዊ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ 9ኛ እና ኤርትራዊው ሳሙኤል ፀጋዬ 16ኛ ደረጃን በመያዝ ማራቶኑን አጠናቀዋል።

በፓኪስታኗ ላሆር ግዛት የሚኖር አንድ ቤተሰብ የሚጠበቅበትን ውዝፍ የመብራት ክፍያ ለመቀበል ከሄዱ የፖሊስ አካልት ጋት በተፈጠረ አምባጓሮ ፖሊሶቹ በድንጋይ ውርወራ ጉዳት ከደረሰባቸው በኋላ በወንጀሉ ተጠርጥረዋል የተባሉ የቤተሰቡ አባላት ክስ ሲመሰረትባቸው ፖሊስ ይህንንም ልጅ በተባባሪ ተጠርጣሪነት በመክሰስ ፍርድ ቤት አቅርበውታል። የ9 ወር ልጅ በመሆኑ ከክሱ ያላመለጠው ህጻን በአያቱ እቅፍ ውስጥ ሆኖ አሻራ በመስጠት የአለማችን ትንሹ ተተርታሪ ወንጀለና ሊሆን በቅቷል።

ክስተቱ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ከተዘገበ እና የህጻናት መብት ተቆርቋሪዎችን ጨምሮ ብዙዎች ካወገዙት በኋላ የልጁን ክስ ያዘጋጀው ባለስልጣን ከስራ የተባረረ ሲሆን በልጁ ላይ የቀረበው ክስ ይቋረጥ አይቋረጥ እስካሁን ምንም የተሰማ ነገር የለም።[CNN]

ምንም አይነት መሳሪያ ሳይጠቀሙ አንድ ግዜ በያዙት አየር ውሃ ውስጥ በመቆየት ያለው ሪከርድ የሚገርም 22 ደቂቃ ሙሉ ነው። ማመን ይከብዳል አይደል?? ብዙዎች ለዚህ ሪከርድ ትኩረት የሰጡት እ.ኤ.አ በ2001 ዓ.ም ማርቲን ስቴፓኒክ የተባለ ዋናተኛ 8 ደቂቃ 6 ሰከንድ ሪከርዱን በመያዝ አለምን ጉድ ካሰኘ በኋላ ነበር። ሪከርዱ በተለያዩ ሰዎች እየተሻሻለ በ2009 ዓ.ም 11 ደቂቃ 35 ሰከንድ ደርሶ ነበር።

የሰው ልጅ ሲተነፍስ ኦክስጅንን አስገብቶ ሰውነቱ ሃይል ካመነጨ በኋላ ሰውነታችን የሚያመነጨው ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ በደማችን ውስጥ ሲገባ ሰውነታቸን አየር እንዲያስወጣ መልክት ይሰጠው እና አየሩን እናስወጣዋለን። ይህንን ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ካላስወጣነው ከ ሳምባችን ጀምሮ ቀስ በቀስ የሚሰራጭ ህመም እራስን መሳት ብሎም እስከሞት ሊያደርስ ይችላል።

እነዚህ ልምድ ያላቸው ዋናተኞች ግን ሰውነታቸው ካርቦን ዳይ ኦክሳይድን የሚያመነጭበት ፍጥነት ረጋ ያለ እና ደማቸው ውስጥ ኦክስጅን የሚያቆዩበት የተለየ መንገድ ስላላቸው ረዘም ያለ ግዜ ምንም ሳይሆኑ ትንፋሻቸውን በሰውነታቸው መያዝ ይችላሉ። አይምሮአቸውን በጣም በማረጋጋት የሚያወጡትን ሃይል የሚቆጥቡ ሲሆን የልብ ምታቸውም በብዙዎች ላይ ከሚታየው በደቂቃ 70 ምት ወደ 30 በማውረድ የኦክስጅን ስርጭታቸውን ሆነ የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ መሰብሰብን ይቀንሱታል።

ቀጣዩ ቪዲዮ ላይ አንድ ኢንዶኔዢያዊ ውሃ ውስጥ ለደቂቃዎች ትንፋሹን መያዝ ብቻ ሳይሆን አሳ ሁላ እንዴት እንደሚያጠምድ ይመልከቱት። [io9]

በአብዛኛው ሃገራት የሰው ልጅ ከዚህ አለም በሞት ሲለይ ቤተሰቦቹ የሃዘናቸውን ግዜ በለቅሶ እና በትካዜ ማሳለፋቸው የተለመደ ነው። ጋና ውስጥ ግን ከዚህ በተለየ ሁኔታ በቤተክርስቲያን የሚካሄደው የቀብር ስነ ስርዓት ከጠነቀቀ በኋላ ሃዘንተኞቹን ለማጽናናት በሚል ከሰርግ ባልተናነሰ ሁኔታ በለቀስተኞቹ ቤት እጅግ ትልቅ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት ያካሂዳሉ። ሲ ኤን ኤን በሁኔታው ላይ የሰራውን ዝግጅት ከታች ካለው ቪዲዮ ይመልከቱ። [CNN]

ይህ የአለማችን ትልቁ የአስዮን ድርሻ ገበያ የሆነው እና በአሜሪካን አገር ኒውዮርክ ከተማ ውስጥ ዎል ስትሪት በሚባል ጎዳና ላይ መሰረቱን ያደረገው የኒውዮርክ አክስዮን ድርሻ መገበያያ ማዕከል ውስጥ የሚሰራ ደላላ ህይወት ላይ ያጠነጠነ ፊልም ነው። በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራውን ይህንን ፊልም ዝነኞቹ ሊዮናርዶ ዲካፕሪዮ እና ማቲው ማኮግንሄይ ይተውኑበታል። የአለምን ኢኮኖሚ የሚነዳው የዚህ ማዕከል አሰራር ትንሽ ማወቅ ከፈለጉ በሚያዝናና መልኩ የሚያሳይ ፊልም ነው። የፊልሙ ማስታወቂያ ይመልከቱት።

Firefox-OS-with-Fox

በተመሳሳይ መጠሪያ የሚጠራ ሞዚላ የተሰኘ የድህረ ገጽ ማሰሻ በመስራት የሚታወቀው ይህ ድርጅት በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎችን በእጅጉ ተጠቃሚ ያደርጋል ብሎ ያመነበተን ይህንን ርካሽ ነገር ግን ዘመናዊ ስልክ ቻይና ውስጥ ከሚገኝ ድርጅት ጋር በጥምረት ለገበያ ለማቅረብ እቅድ ይዟል። ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በባርሴሎና በተካሄደ የተንቀሳቃሽ ስልኮች አውደ ርዕይ ላይ ይህንን እቅዱን ይፋ ያደረገው ሞዚላ ስልኩ በውድ ዋጋ እንደሚሸጡት ስልኮች ትልቅ ብቃት ባይኖረውም ኢንተርኔት አገልግሎት እና ሌሎች ፕሮግራሞችን ለመጫን እና የመጀመሪያ ግዜ ገዢዎችን በቀጥታ ከኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ያስተዋውቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በሃገራችን ጨምሮ በብዛት በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የሚኖሩ ሰዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ለመጀመሪያ ግዜ ሲጠቀሙ በዋጋ አነስ ብሎ ግን ለስልክ እና ለአጭር መልክት መለዋወጫ ውጪ ብዙ አገልጎት የማይሰጡ ስልኮችን ይጠቀማሉ። የዚህ ስልክ ወደ ገበያ መምጣት ሰዎች ኢንተርኔት ቴክኖሎጂን በኮምፒውተር ከመጠቀማቸው ቀድመው በስልካቸው እንዲተዋወቁት የሚያደርግ ሲሆን ከኢንተርኔት ውጪ የሚዘጋጁ ፕሮግራሞችን በመጠቀም ብዙ አገልግሎት ከስልኩ እንደሚያገኙ ይጠበቃል።[BBC]

Follow

Get every new post delivered to your Inbox.

Join 276 other followers